የአጠቃቀም መመሪያ

አካውንት ከመክፈት ጀምሮ መጽሐፍ እስከ መግዛትና ማንበብ፣ የተፈጥሮ መዝገቡን እስከ ማሰስ፣ ሱቅ ከፍተው ሥራዎን እስከ መሸጥና ገቢዎን እስከ ማስላት ድረስ በቅደም ተከተል። ምስሎቹ በሙሉ ከድረ-ገጹ በቀጥታ የተነሱ ናቸው።

የተሻሻለው፦ ኅዳር 6 ቀን 2019 ዓ.ም. (Nov 15, 2026)

PDF ያውርዱ

መግቢያ#

1. መመሪያውን እንዴት እንደሚያነቡ#

ድረ-ገጹ የሚሠራው በእንግሊዝኛ ነው። ይህ መመሪያ በስክሪኑ ላይ የሚያዩትን የእንግሊዝኛ ቃል እንዳለ ያሳያል፤ ትርጉሙንና ምን ማድረግ እንዳለብዎ ደግሞ በአማርኛ ያብራራል። ምስሎቹ በሙሉ ከ www.thearkiveofnoah.com በቀጥታ የተነሱ ናቸው።

በመመሪያው ውስጥትርጉሙ
Sign inበስክሪኑ ላይ ያለ ቁልፍ፣ ርዕስ ወይም የሳጥን ስም። በስክሪኑ ላይ በዚሁ ፊደል ይፈልጉት።
3በምስሉ ላይ በቀይ የተከበበ ቦታ። ከምስሉ ሥር ያለው ዝርዝር ተመሳሳይ ቁጥር ያለውን ቦታ ያብራራል።
ጥቁር ክብ ውስጥ ያለ ቁጥርበቅደም ተከተል የሚፈጸም እርምጃ።
ምክር፦ጠቃሚ አቋራጭ ወይም ጊዜ የሚቆጥብ ዘዴ።
ጥንቃቄ፦ገንዘብ ወይም መረጃ እንዳይጠፋ የሚያስጠነቅቅ።
ማስታወሻ፦ለመረዳት የሚያግዝ ተጨማሪ መረጃ።

በምስሎቹ ላይ የሚታዩት «Reader Demo» እና «Demo Nature Shop» ለዚህ መመሪያ ብቻ የተዘጋጁ የሙከራ ስሞች ናቸው፤ ዋጋዎችና ቁጥሮችም ምሳሌ ናቸው። የእርስዎ ስክሪን የራስዎን መረጃ ያሳያል።

2. ፈጣን ጅምር፦ ከየት ልጀምር?#

ለሁሉም ተጠቃሚ#

3. ድረ-ገጹን ማወቅ#

በየትኛውም ገጽ ላይ ቢሆኑም በላይ ያለው ምናሌ አንድ ነው።

የመነሻ ገጹ ምናሌ፤ Shop፣ Contact፣ Sign in እና Browse በቀይ ተከብበዋል(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
የመነሻ ገጽ እና ዋናው ምናሌ
  • 1Shop፦ የሁሉም ሱቆች ገበያ (The Exchange)
  • 2Contact፦ አርካይቭን ለማግኘት
  • 3Sign in፦ መግቢያ ወይም አዲስ አካውንት
  • 4Browse፦ ቀጥታ ወደ የተፈጥሮ መዝገቡ
በምናሌው ላይየሚወስድዎ ቦታ
Homeየመነሻ ገጽ፤ ወደ ታች ሲወርዱ የተፈጥሮ መዝገቡ (Explore the natural world) ይገኛል።
Work with Usከአርካይቭ ጋር ስለ መሥራት መረጃ።
Contributorsከአርካይቭ ጀርባ ያሉ ደራሲዎችና ሻጮች።
የጨረቃ ምልክትጨለማ ገጽታ (Dark mode)፤ እንደገና ሲጫኑት ይመለሳል፤ ምርጫዎ ይታወሳል።
የቦርሳ ምልክትጋሪዎ (Your cart)።
የገጹ ግርጌContributors፣ Terms፣ Privacy፣ Blog እና User guide (ይህ መመሪያ)።

4. አካውንት መክፈትና መግባት#

የገዙትን መጽሐፍ ለማንበብ፣ ከ20 በላይ ዝርያዎችን ለማየት ወይም ሱቅ ለመክፈት አካውንት ያስፈልግዎታል (መግዛት ግን ያለ አካውንትም ይቻላል)። መክፈት ነጻ ነው፤ አንድ ደቂቃ ያህል ይወስዳል።

አዲስ አካውንት (Sign up)

ከላይ በቀኝ Sign in ይጫኑ፤ ከሥር Don't have an account? አጠገብ ያለውን Sign up ይጫኑ። ቅጹን ከላይ ወደ ታች ይሙሉ፦

  • 1First name፦ ስምዎ
  • 2Last name፦ የአባትዎ ስም
  • 3Email፦ ግዢዎችዎ የሚመዘገቡበት ኢሜይል
  • 4Username (optional)፦ ግዴታ አይደለም፤ ከመረጡ 3 እስከ 30 ቁምፊ፣ ትንንሽ የእንግሊዝኛ ፊደላት፣ ቁጥሮች፣ _ እና - ብቻ
  • 5Password፦ የይለፍ ቃል
  • 6አራቱ መስፈርቶች፦ ቢያንስ 6 ቁምፊ፣ አንድ ትንሽ ፊደል፣ አንድ ትልቅ ፊደል፣ አንድ ቁጥር። ሲሟሉ ምልክታቸው ይቀየራል።
  • 7ደንቦቹንና የግላዊነት ፖሊሲውን መቀበልዎን ለማሳየት ክቡን ይጫኑ
  • 8Create account፦ አካውንቱ ወዲያውኑ ይከፈታል
የምዝገባ ቅጽ፦ ስም፣ ኢሜይል፣ የተጠቃሚ ስም፣ የይለፍ ቃል፣ መስፈርቶች፣ የስምምነት ክብና Create account(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
Create your account

መግባትና የተረሳ የይለፍ ቃል

የመግቢያ ገጽ፦ የኢሜይል ሳጥን፣ የይለፍ ቃል፣ Forgot?፣ Sign in እና Sign up(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
የመግቢያ ገጽ
  • 1ኢሜይል ወይም username
  • 2የይለፍ ቃል
  • 3Forgot?፦ የይለፍ ቃል መቀየሪያ አገናኝ በኢሜይል ይላካል
  • 4Sign in፦ መግባት
  • 5Sign up፦ አዲስ አካውንት

ከገቡ በኋላ ከላይ በቀኝ የስምዎ የመጀመሪያ ፊደላት ያሉበት ክብ ይታያል።

የይለፍ ቃል መቀየር#

ከፕሮፋይል ምናሌው Password & security ይምረጡ። የይለፍ ቃል ሲቀይሩ ከሌሎች መሣሪያዎች ሁሉ ይወጣሉ።

Password and security ገጽ፦ የአሁኑ የይለፍ ቃል፣ Reset by email፣ አዲስ የይለፍ ቃል፣ ማረጋገጫ እና Update password(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
Password & security
  • 1Current password፦ የአሁኑ የይለፍ ቃል
  • 2Reset by email፦ የአሁኑን ከረሱ በኢሜይል መቀየሪያ
  • 3New password፦ አዲሱ የይለፍ ቃል (አራቱ መስፈርቶች ይመለከታሉ)
  • 4Confirm new password፦ አዲሱን ደግመው ይጻፉ
  • 5Update password፦ ያስቀምጣል
ምክር፦የመቀየሪያ ኢሜይሉ ካልደረሰ የSpam ወይም የPromotions ማህደርን ይመልከቱ።

5. የአካውንት ምናሌ#

ከገቡ በኋላ ከላይ በቀኝ ያለውን የስምዎ ፊደላት ያሉበትን ክብ 1 ሲጫኑ ይህ ዝርዝር ይወርዳል።

የአካውንት ምናሌ ተከፍቶ ሰባቱ አማራጮች ተቆጥረዋል(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
የፕሮፋይል ምናሌ
  • 2My account፦ የአካውንትዎ መረጃ
  • 3My library፦ የገዟቸው መጻሕፍትና ፋይሎች (ላይብረሪ)
  • 4My orders፦ ያዘዟቸው ትዕዛዞችና ደረሰኞች
  • 5Arkive Pass፦ የተፈጥሮ መዝገቡን የሚከፍተው ማለፊያ
  • 6Password & security፦ የይለፍ ቃል መቀየሪያ
  • 7Sell on the Exchange፦ ሱቅ ለመክፈት ማመልከቻ
  • 8Sign out፦ ከአካውንት መውጣት
ጥንቃቄ፦በጋራ ወይም በሕዝብ ኮምፒዩተር ከተጠቀሙ ሲጨርሱ ሁልጊዜ Sign out ይጫኑ።

ሱቅዎ ከጸደቀ በኋላ የሥራ ቦታዎ (Studio) በ www.thearkiveofnoah.com/studio ይገኛል፤ አድራሻውን በአሳሽዎ ላይ ምልክት ያድርጉት።

6. መፈለግ፣ መግዛትና መክፈል#

እያንዳንዱ ምርት እስከ ሁለት ዋጋ ሊኖረው ይችላል፦ በኢትዮጵያ በብር በChapa፣ ከኢትዮጵያ ውጭ በዶላር በካርድ። ሁለቱ ዋጋዎች እርስ በርስ አይመነዘሩም፤ ሻጩ ለየብቻ ይወስናቸዋል። አንዱ ብቻ ካለ ምርቱ በዚያ ገንዘብ ብቻ ይሸጣል።

የሚፈልጉትን ማግኘት (The Exchange)

The Exchange ገጽ፦ የምድብ መምረጫ፣ የፍለጋ ሳጥን፣ Filters፣ Sort by እና የምርት ካርድ(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
The Exchange፦ እዚህ «Digital products» ምድብ ተመርጧል
  • 1የምድብ መምረጫ፦ All፣ Ebooks፣ Digital products፣ Seeds & Seedlings…
  • 2የፍለጋ ሳጥን፦ የመጽሐፉን ወይም የምርቱን ስም ይጻፉ
  • 3Search፦ ፍለጋውን ያስጀምራል
  • 4Sell on the Exchange፦ የራስዎን ሱቅ ለመክፈት
  • 5Filters፦ ተጨማሪ ማጣሪያዎች
  • 6Sort by፦ በዋጋ ወይም በስም መደርደር
  • 7የምርት ካርድ፦ ሻጩ፣ ምድቡ፣ የዶላርና የብር ዋጋ
በካርዱ ላይ ያለ ምልክትትርጉሙ
COMING SOONገና ለሽያጭ አልቀረበም፤ መግዛት አይቻልም።
Read onlineበአርካይቭ አንባቢ ውስጥ የሚነበብ ኢ-መጽሐፍ።
DIGITALከከፈሉ በኋላ ወዲያውኑ የሚያወርዱት ፋይል።
SAVE 50%ቅናሽ፤ የቀድሞው ዋጋ ተሰርዞ ከጎኑ ይታያል።

የመጽሐፉ ገጽ

የመጽሐፍ ገጽ፦ የዶላርና የብር ዋጋ፣ Add to cart፣ Buy now፣ Share እና Support(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
የመጽሐፍ ገጽ (የደራሲው ስም ሆን ተብሎ ደብዝዟል)
  • 1የዶላር ዋጋ (በካርድ ለሚከፍሉ)
  • 2የብር ዋጋ (በChapa ለሚከፍሉ)
  • 3Add to cart፦ ወደ ጋሪ መጨመር
  • 4Buy now፦ አሁኑኑ መግዛት
  • 5Share this book፦ አድራሻውን ለሌሎች ማጋራት
  • 6Support እና የሱቁ ስም፦ ለሻጩ ድጋፍ (Tips)
  • 7About this book፦ የመጽሐፉ መግለጫ
  • 8የአንባቢዎች የኮከብ ምዘና (ግምገማ መጻፍ)

ሱቅን መከተልና ግምገማ መጻፍ#

  1. በመጽሐፉ ገጽ የሱቁን ስም (by …) ይጫኑ፤ የሱቁ ገጽ ይከፈታል። Follow ሲጫኑ ሱቁ አዲስ ሥራ ሲያወጣ ያውቃሉ።
  2. የገዙትን መጽሐፍ ገጽ ይክፈቱ፤ ወደ Ratings & reviews ይውረዱ፤ Write a review ይጫኑ።
  3. ከ1 እስከ 5 ኮከብ ይምረጡ፤ ከፈለጉ አጭር አስተያየት ይጻፉ፤ ያስቀምጡ። በኋላ Update your review ብለው መቀየር ይችላሉ።
ማስታወሻ፦የኮከብ ምዘናና አስተያየት መስጠት የሚችሉት መጽሐፉን የገዙ ብቻ ናቸው።
ማስታወሻ፦Lifetime access in your library · no download ማለት መጽሐፉ ለዘለቄታው በላይብረሪዎ ይኖራል፤ በስልክ፣ በታብሌትና በኮምፒዩተር ያነቡታል።

መክፈል

  1. Your cart ይከፈታል። ካልገቡ (እንግዳ ከሆኑ) 1 Your email ላይ ኢሜይልዎን በትክክል ያስገቡ፤ መጽሐፉ የሚደርሰው ለዚህ ኢሜይል ነው። ከገቡ ይህ ሳጥን አይታይም፤ ግዢው በቀጥታ ወደ አካውንትዎ ይመዘገባል።
  2. ከኢትዮጵያ ውጭ ከሆኑ 2 Pay $6.00 · International (ዋጋው እንደ ምርቱ ይለያል) ይጫኑ፤ በVisa፣ Mastercard ወይም Amex በዶላር ይከፍላሉ።
  3. በኢትዮጵያ ውስጥ ከሆኑ 3 Pay ብር 150.00 · In Ethiopia ይጫኑ፤ በChapa ገጽ ላይ ከሚቀርቡት አማራጮች መርጠው በብር ይከፍላሉ።
  4. ክፍያው ሲሳካ Payment successful ገጽ ይመጣል። በChapa ከከፈሉ View Chapa receipt ደረሰኝዎን ያሳያል።
  5. ለማንበብ Sign in to read ይጫኑ፤ በገዙበት ኢሜይል ይግቡ። ያዘዟቸውን ሁሉ በኋላ በMy orders ያገኛሉ።
ጥንቃቄ፦ኢሜይሉ ከተሳሳተ መጽሐፉ ወደ ሌላ ሰው አካውንት ይመዘገባል። ከመክፈልዎ በፊት ደግመው ያረጋግጡ።
ማስታወሻ፦እንግዳ ከሆኑ ኢሜይል እስኪያስገቡ ድረስ ሁለቱ የክፍያ ቁልፎች አይሠሩም። አንድ ምርት በአንዱ ገንዘብ ብቻ ዋጋ ካለው የሌላኛው ቁልፍ ምክንያቱን ከሥሩ ይጽፋል።
ጋሪ፦ የኢሜይል ሳጥንና ሁለቱ የክፍያ ቁልፎች(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
ጋሪና ሁለቱ የክፍያ መንገዶች

7. ላይብረሪና የአርካይቭ አንባቢ#

የገዟቸው መጻሕፍትና ዲጂታል ፋይሎች በሙሉ በMy Library ይቀመጣሉ። ከፕሮፋይል ምናሌው My library ይምረጡ።

ባዶ My Library ገጽና Browse the shop ቁልፍ(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
My Library (ገና ግዢ ያልተፈጸመበት አካውንት)
  • 1My Library፦ የገዙትና የጻፉት ሁሉ
  • 2ባዶ ከሆነ ይህ መልእክት ይታያል
  • 3Browse the shop፦ ወደ ገበያው

መጽሐፍ ማንበብ ወይም ፋይል ማውረድ#

  1. ለማንበብ የመጽሐፉን ሽፋን ይጫኑ፤ መጽሐፉ በአንባቢው ይከፈታል።
  2. ዲጂታል ምርት ከሆነ Download ወይም Download files ይጫኑ፤ የምርቱ ገጽ ይከፈታል።
  3. በፋይሎቹ ዝርዝር ውስጥ የሚፈልጉትን ፋይል ይጫኑ፤ ማውረዱ ይጀምራል። አገናኞች (Canva፣ Google Sheets) እዚያው ይታያሉ።
  4. በግዢ ጊዜ ባስገቡት ኢሜይልም ወደ ምርቱ የሚወስድ አገናኝ ይደርስዎታል፤ ፋይሎቹን ከዚያ ያወርዳሉ።
ማስታወሻ፦ለደኅንነት ሲባል እያንዳንዱ የማውረጃ አገናኝ ለ10 ደቂቃ ብቻ ይሠራል። ጊዜው ካለፈ ፋይሉን እንደገና ይጫኑ፤ አዲስ አገናኝ ይፈጠራል።

የአንባቢው መሣሪያዎች

የአንባቢው የመሣሪያ መስመር፤ ዘጠኝ ቁልፎች ተቆጥረው(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
የአርካይቭ አንባቢ፦ የመሣሪያዎቹ መስመር ከላይ ይታያል
ቁ.ምልክትምን ያደርጋል
1← ቁጥር →ወደ ኋላና ወደ ፊት፤ መካከል ያለው ቁጥር ያሉበት ገጽ ነው
2Tየፊደል መጠን፣ የመስመር ክፍተትና የፊደል ዓይነት
3ማጉያ መነጽርበመጽሐፉ ውስጥ ቃል መፈለግ
4ፀሐይየገጹ ቀለምና ብርሃን፦ Light፣ Sepia፣ Dark
5ሁለት ዓምድየንባብ ሁነታ፦ Scroll ወይም Page
6ዝርዝር መስመሮችማውጫ፤ የምዕራፍ ስም ሲጫኑ ወደዚያ ይወስዳል
7ዕልባትያሉበትን ቦታ ምልክት ማድረግ (Bookmarks)
8ብዕርያደመቋቸውና ማስታወሻዎች (Highlights)
9አራት ቀስትሙሉ ስክሪን

በመስመሩ ላይ ያሉት ሌሎች ሁለት ምልክቶች፦ ኮምፓሱ (Go to) ወደ አንድ ገጽ በቀጥታ ይወስዳል፤ የጥያቄ ምልክቱ (Help) አጭር ማብራሪያ ያሳያል።

Scroll ወይም Page፦ የንባብ ሁነታ#

የንባብ ሁነታ መምረጫ፦ Scroll፣ Page እና Single(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
Reading mode መምረጫ
  • 1የሁለት ዓምድ ምልክቱ፦ መምረጫውን ይከፍታል
  • 2Scroll፦ ሳይቋረጥ ወደ ታች (ነባሪ)
  • 3Page፦ ገጽ በገጽ መገልበጥ
  • 4Single አንድ ገጽ፣ Double ሁለት ገጽ፣ Auto እንደ ስክሪኑ

መጽሐፍ ሲከፈት በነባሪነት Scroll ሁነታ ነው፦ ገጹ ሳይቋረጥ ወደ ታች ይወርዳል።

ምክር፦Page ከመረጡ ምርጫዎ በዚያው መሣሪያ ይታወሳል፤ በሚቀጥለው ጊዜ በPage ይከፈታል።

ማድመቅ፣ ማስታወሻና በሌላ መሣሪያ መቀጠል

  • ለማድመቅ ዓረፍተ ነገሩን ይምረጡ (በስልክ ጣትዎን በቃሉ ላይ ትንሽ ያቆዩ፣ ከዚያ ይጎትቱ)፤ የሚመጣውን የቀለም መስመር ይንኩ።
  • በደመቀው ጽሑፍ ላይ ማስታወሻ ለመጻፍ በምስሉ 8 Highlights ይክፈቱ።
  • የደረሱበት ቦታ፣ ዕልባቶች፣ ያደመቋቸውና ማስታወሻዎች ከአካውንትዎ ጋር ይቀመጣሉ፤ በሌላ መሣሪያ ሲገቡ ካቆሙበት ይቀጥላሉ። ኢንተርኔት ባይኖርም ይመዘገባሉ፤ መስመር ሲመለስ ይመሳሰላሉ።
ማስታወሻ፦የደራሲዎችን መብት ለመጠበቅ ጽሑፍ መቅዳት አይፈቀድም፤ በገጹ ላይ የአካውንትዎ ደብዛዛ ምልክት ይታያል።

8. የተፈጥሮ መዝገብና Arkive Pass#

የአርካይቭ ልብ የተፈጥሮ መዝገቡ ነው፦ ከ142 ሺህ በላይ ዝርያዎች በአምስት ምድብ (ዕፅዋት፣ እንስሳት፣ ፈንገሶች፣ አልጌዎችና ንጥረ ነገሮች)። በምናሌው Browse ይጫኑ፤ ወይም በመነሻ ገጹ ወደ ታች ይውረዱ።

የተፈጥሮ መዝገብ፦ የፍለጋ ሳጥን፣ የመደርደሪያ ቁልፎች፣ ምድቦች፣ Region፣ Rarity እና የዝርያ ካርድ(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
Explore the natural world
  • 1የዝርያውን ስም ወይም ሳይንሳዊ ስሙን ይጻፉ። አቋራጭ፦ Ctrl + K (በMac ⌘ K)
  • 2Trending · Newest · A - Z፦ ተወዳጅ · አዲስ · በፊደል
  • 3Refine፦ ተጨማሪ ማጣሪያዎች
  • 4Plants · Animals · Fungi · Algae · Elements፦ ምድቦቹ፤ ቁጥሩ የዝርያ ብዛት ነው
  • 5Region፦ በክልል ማጣራት
  • 6Rarity፦ Common፣ Uncommon፣ Rare፣ Legendary
  • 7የዝርያ ካርድ፦ ሲጫኑ የዝርያው ገጽ ይከፈታል
እርስዎበነጻ የሚያዩትከዚያ በላይ ለማየት
ሳይገቡ (እንግዳ)20 ዝርያነጻ አካውንት ይክፈቱ
ነጻ አካውንት ይዘው100 ዝርያArkive Pass ይግዙ
Arkive Pass ይዘውሁሉንምየእያንዳንዱ ዝርያ ሙሉ መዝገብ ጭምር

Arkive Pass

100 ዝርያዎችን ካዩ በኋላ You've explored your 100 free species («100 ነጻ ዝርያዎችዎን አይተው ጨርሰዋል») የሚል መልእክትና Get the Arkive Pass ቁልፍ ይመጣል። እያንዳንዱ የዝርያ ገጽም መጀመሪያ ነጻ ቅድመ ዕይታ ብቻ ያሳያል።

የArkive Pass ገጽ፦ የቀንና የ30 ቀን ዋጋ ከሁለቱ የመግዣ ቁልፎች ጋር(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
የArkive Pass ገጽ (ከገቡ በኋላ)
  • 1ዋጋ፦ በቀን 2.99 ብር ወይም ለ30 ቀን 89.70 ብር
  • 230-day pass፦ ለ30 ቀን
  • 3Day pass፦ ለአንድ ቀን
  1. ወደ አካውንትዎ ይግቡ፤ ከፕሮፋይል ምናሌው Arkive Pass ይምረጡ።
  2. የሚፈልጉትን ጊዜ ይጫኑ።
  3. ክፍያውን በChapa በብር ያጠናቅቁ፤ ሙሉ መዝገቡ ወዲያውኑ ይከፈታል።
የትኛውን ልግዛ?ዋጋበቀንለማን ይመረጣል
Day pass2.99 ብር2.99 ብርለአንድ ጥናት ወይም የቤት ሥራ አንድ ቀን ብቻ ለሚፈልግ
30-day pass89.70 ብር2.99 ብርበየቀኑ ማለት ይቻላል ለሚጠቀም፤ በየቀኑ መግዛት አያስፈልግም
ምክር፦የ30 ቀን Arkive Pass ከ30 የቀን Arkive Pass ጋር እኩል ዋጋ ነው (30 × 2.99 = 89.70 ብር)፤ ቅናሽ የለውም። በወር ውስጥ ጥቂት ቀናት ብቻ የሚጠቀሙ ከሆነ በሚፈልጉበት ቀን Day pass መግዛት ይቀልላል፤ ለምሳሌ 10 ቀን ብቻ ከተጠቀሙ 29.90 ብር ይከፍላሉ።
ማስታወሻ፦ክፍያው በራሱ አይታደስም፤ ሳይፈልጉ አይከፈልዎትም። ጊዜው ሳያልቅ ካደሱ አዲሶቹ ቀናት በቀሪዎቹ ላይ ይደመራሉ።

ሙሉ መዝገቡ የሚያካትተው፦ ባሕርያት፣ መኖሪያና ሥርጭት፣ ሥነ ሕይወት፣ ሳይንሳዊ ምደባ፣ የጥበቃ ሁኔታ፣ መራባት፣ ጥቅምና ደኅንነት (መርዛማነትን ጨምሮ)።

9. ሱቅን መደገፍ (Tips)#

የአንድን ሱቅ (ደራሲ ወይም ሻጭ) ሥራ ከወደዱ በፈቃድዎ ድጋፍ መስጠት ይችላሉ። ከድጋፉ 80% በቀጥታ ለሱቁ ባለቤት ይደርሳል። በመጽሐፉ ገጽ ወይም በሱቁ ገጽ ላይ Support (ከሱቁ ስም ጋር) ይጫኑ።

የድጋፍ መስኮት፦ ገንዘብ፣ መጠኖች፣ ሌላ መጠን፣ መልእክት፣ ስም እና Tip ቁልፍ(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
የድጋፍ መስኮት
  • 1ገንዘቡ፦ USD (በካርድ) ወይም ETB (በChapa)
  • 2ከቀረቡት መጠኖች አንዱ
  • 3Another amount፦ የራስዎ መጠን
  • 4መልእክት (ግዴታ አይደለም)፤ በሱቁ ገጽ ላይ ለሁሉም ይታያል
  • 5Your name (optional)፤ ባዶ ከተዉት «A supporter» ተብሎ ይታያል
  • 6Tip፦ ክፍያውን ያጠናቅቃል
ማስታወሻ፦በሱቁ ገጽ ላይ መልእክት የሚታየው ክፍያው የተረጋገጠ ድጋፍ ሲሆን ብቻ ነው። እንግዳ ሆነው ከሰጡ በኋላ በዚያው ኢሜይል አካውንት ቢከፍቱም መብቱ ይቀጥላል።

ለደራሲዎችና ለሻጮች#

10. ሱቅ መክፈት#

መጻሕፍትንና ዲጂታል ምርቶችን (አካላዊ ዕቃዎች በቅርቡ) ለመሸጥ የራስዎ ሱቅ ያስፈልግዎታል። መክፈት ነጻ ነው፤ እያንዳንዱ ማመልከቻ በአርካይቭ አስተዳዳሪ ይገመገማል። ከፕሮፋይል ምናሌው Sell on the Exchange ይምረጡ (ይህ ቁልፍ በShop ገጽ አናት ላይም አለ)። ቅጹ አራት ክፍሎች አሉት።

1 · የኮሚሽን መግለጫና ሱቅዎ (Your shop)

Open a shop ገጽ፦ የኮሚሽን መግለጫ፣ የሚፈቀዱ ፋይሎች፣ የሱቅ ስምና Tagline(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
Open a shop
  • 1የኮሚሽን መግለጫ፦ Free 35%፣ Pro (299 ብር በወር) 15%፣ Premium (499 ብር በወር) 10%
  • 2የሚፈቀዱ የመጽሐፍ ፋይሎች፦ EPUB (ተመራጭ) እና Word (.docx)። PDF ለመስመር ላይ ንባብ አይፈቀድም፤ እንደ ዲጂታል ምርት ይሸጣል
  • 3Shop name፦ የሱቁ ስም፤ አድራሻው (/author/…) ከዚህ በራሱ ይዘጋጃል
  • 4Tagline (optional)፦ ሱቁን በአንድ ዓረፍተ ነገር የሚገልጽ

2 · ስለ እርስዎ (About you)

About you ክፍል፦ ፎቶ፣ ስም፣ ስልክ፣ አገር፣ ከተማ፣ Bio እና Facebook(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
About you
  • 1Profile photo፦ ግዴታ ነው፤ ፊትዎ በግልጽ የሚታይበት፣ እንደ ፓስፖርት ፎቶ
  • 2First name፦ ስም
  • 3Last name፦ የአባት ስም
  • 4Phone number፦ ከአገር ኮድ ጋር (+251…)
  • 5Country፦ አገር
  • 6City፦ ከተማ
  • 7Bio (optional)፦ ስለ እርስዎ አጭር መግለጫ
  • 8Links & socials፦ ያለዎትን ብቻ ይሙሉ
ምክር፦ግልጽ ፎቶና የተሟላ መግለጫ ማመልከቻዎ ቶሎ እንዲጸድቅ፣ ገዢዎችም እንዲያምኑዎት ይረዳሉ።

3 · ገቢዎ እንዴት እንደሚደርስዎ (How you'll be paid)

የገቢ ክፍያ በየሁለት ሳምንቱ ይላካል። ይህን ክፍል በኋላ መሙላት ይቻላል፤ አሁን ከሞሉት የመጀመሪያ የገቢ ክፍያዎ አይዘገይም።

How you will be paid ክፍል፦ የባንክ አገር፣ የክፍያ መንገድና የሒሳብ መረጃ(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
የባንክ መረጃ
  • 1I bank in Ethiopia፦ በኢትዮጵያ
  • 2I bank outside Ethiopia፦ ከኢትዮጵያ ውጭ (Zelle ወይም ዓለም አቀፍ ዝውውር)
  • 3Commercial Bank of Ethiopia (CBE)፦ ንግድ ባንክ
  • 4Bank transfer፦ ለሌላ ባንክ
  • 5Account holder's full name፦ ልክ በባንክ ደብተሩ ላይ እንዳለ
  • 6Bank name፦ የባንኩ ስም
  • 7Account number፦ የሒሳብ ቁጥር
  • 8Branch (optional)፦ ቅርንጫፍ
ጥንቃቄ፦የሒሳብ ቁጥሩን ደግመው ያረጋግጡ፤ ወደ ተሳሳተ ሒሳብ የተላከ ገንዘብ መመለስ አይቻልም። ይህ መረጃ በግል ይቀመጣል፤ በሱቅዎ የሕዝብ ገጽ ላይ አይታይም።

4 · የሻጮች ስምምነት (Seller agreement)

Seller Agreement፦ አማርኛ ቁልፍ፣ ሙሉ ስምምነት፣ የስምምነት ክብና Submit application(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
Seller Agreement እና Submit application
  • 1ስምምነቱን በአማርኛ ለማንበብ አማርኛ ይጫኑ
  • 2Read the full Seller Agreement፦ ሙሉ ስምምነቱ
  • 3ከተስማሙ ክቡን ይጫኑ (35% ኮሚሽን፣ በየሁለት ሳምንቱ የገቢ ክፍያ)
  • 4Submit application፦ ማመልከቻውን ይልካል

ማመልከቻዎ ሲጸድቅ ሱቅዎ ይከፈታል፤ አድራሻውን ቀድተው ለአንባቢዎችዎ ማጋራት ይችላሉ።

11. Studio፦ የሱቅዎ የሥራ ቦታ#

ሱቅዎ ከጸደቀ በኋላ ሁሉንም ሥራ የሚያከናውኑት በStudio ውስጥ ነው።

Studio Dashboard፦ የሱቅ አገናኝ፣ ምናሌ፣ የዶላርና የብር ሒሳቦች(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
Studio Dashboard
  • 1View public shop፦ ሱቅዎ ለሕዝብ እንዴት እንደሚታይ
  • 2የStudio ክፍሎች ምናሌ (ከታች ያለው ሠንጠረዥ)
  • 3USD balance፦ በካርድ ሽያጭ የተገኘ የዶላር ገቢ ሒሳብ
  • 4ETB balance፦ በChapa ሽያጭ የተገኘ የብር ገቢ ሒሳብ
  • 5Pending payout፦ ለእርስዎ ሊከፈል የሚጠብቅ
ክፍልየሚሠራበት
Dashboardገቢ፣ የገቢ ክፍያዎችና በመጽሐፍ የተገኘ ሽያጭ
Booksኢ-መጻሕፍት
Digital productsየሚወርዱ ምርቶች
Productsአካላዊ ዕቃዎችና መላኪያ
Ordersየደረሱ ትዕዛዞች
Tipsድጋፎች
Plans & growthዕቅድ፣ Spotlight፣ ስኬቶች
Shop settingsመገለጫ፣ የገቢ ክፍያ መቀበያና ግብር
በገቢ ሳጥኑ ላይትርጉሙ
Pending payoutለመከፈል የሚጠብቅ ገንዘብ
In progressበመላክ ላይ ያለ የገቢ ክፍያ
Paid outእስካሁን የተከፈለዎት
Total earnedጠቅላላ ያገኙት
grossገዢዎች የከፈሉት ጠቅላላ
platform commissionአርካይቭ የወሰደው ኮሚሽን
ማስታወሻ፦የዶላርና የብር ገቢዎች ለየብቻ ይያዛሉ፤ እርስ በርስ አይመነዘሩም፤ እያንዳንዱ በራሱ ገንዘብ ይከፈላል። Payout history የተላኩልዎትን የገቢ ክፍያዎች ይዘረዝራል።

12. መጽሐፍ ማሳተም#

ሁለት ነገር ያስፈልግዎታል፦ የመጽሐፉ ፋይል (EPUB ወይም Word .docx) እና የሽፋን ምስል። በStudio ውስጥ Books ይክፈቱ፤ + New book ይጫኑ።

New book ቅጽ የላይኛው ክፍል፦ ርዕስ፣ ንዑስ ርዕስ፣ መግለጫ፣ ሽፋን፣ ዋጋዎች፣ ገጾችና You earn(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
New book (የላይኛው ክፍል)
  • 1Title፦ ርዕስ፤ የመጽሐፉ አድራሻ ከርዕሱ ይዘጋጃል
  • 2Subtitle፦ ንዑስ ርዕስ
  • 3Description፦ ስለ ምን እንደሆነና አንባቢ ምን እንደሚያገኝ
  • 4Cover image፦ Upload image (ግዴታ)። 3D cover ግዴታ አይደለም
  • 5Price ($)፦ የዶላር ዋጋ
  • 6Price (ብር)፦ የብር ዋጋ
  • 7Pages፦ የገጽ ብዛት
  • 8You earn፦ ከእያንዳንዱ ሽያጭ የሚደርስዎ፣ ኮሚሽንና 3% የክፍያ ማስኬጃ ተቀንሶ
በስክሪኑ ላይትርጉሙ
Was ($) / Was (ብር)የቀድሞ ዋጋ፤ ከሞሉት ተሰርዞ ይታያል፣ የቅናሽ ምልክትም ይወጣል
አንዱን ዋጋ ባዶ መተውበሌላው ገንዘብ ብቻ ይሸጣል
0መጽሐፉ በነጻ ይቀርባል
ማስታወሻ፦በምስሉ ያለው ምሳሌ የFree ዕቅድ ነው፦ ገዢው $24.00 ይከፍላል፤ 35% ኮሚሽን ($8.40) እና 3% ማስኬጃ ($0.72) ተቀንሶ ደራሲው $14.88 ያገኛል፤ በብር 799 ሲሸጥ 495.38 ብር። ዕቅድዎ ሲቀየር ይህ ቁጥር በራሱ ይስተካከላል (የገቢ ስሌት)።

ፋይሉና ማሳተም

  • 1Formats፦ የፋይል ዓይነቶች ዝርዝር (በነባሪ DOCX, EPUB)
  • 2Upload EPUB / Word፦ የመጽሐፉ ፋይል። Word ሲጫን በራሱ ወደ EPUB ይቀየራል፤ ስንት ምዕራፍ እንደተገኘም ይታያል
  • 3Arkive kingdom link፦ መጽሐፉ የሚዛመደው የተፈጥሮ ምድብ (ለምሳሌ Plants)፤ በዚያ ምድብ ዝርያ ገጾች ሁሉ ላይ በነጻ ይተዋወቃል። ካልተዛመደ None / general (shop only)
  • 4Status፦ Draft (ለሕዝብ የማይታይ) ወይም Published (የታተመ)
  • 5Coming Soon፦ ፋይሉ ሳይዘጋጅ አስቀድሞ ለማስተዋወቅ
  • 6Save book፦ ያስቀምጣል
New book ቅጽ የታችኛው ክፍል፦ Formats፣ ፋይል መጫኛ፣ kingdom link፣ Status፣ Coming Soon እና Save book(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
New book (የታችኛው ክፍል)

ከታተመ በኋላ በBooks ዝርዝር በእያንዳንዱ መጽሐፍ በቀኝ ሦስት ቁልፎች አሉ፦ Preview(በአንባቢው ማየት)፣ የእርሳስ ምልክት (ማስተካከል) እና የቆሻሻ ቅርጫት (መሰረዝ)።

የWord ፋይል ለሚጠቀሙ፦ የማረጋገጫ ዝርዝር#

ያረጋግጡካልተደረገ የሚከሰተው
የምዕራፍ ርዕሶች በHeading 1 ስታይልማውጫው ባዶ ይሆናል ወይም ምዕራፎች ይጠፋሉ
ንዑስ ርዕሶች በHeading 2ንዑስ ክፍሎች በማውጫው ላይ አይታዩም
ባዶ መስመር ላይ የHeading ስታይል የለምስም አልባ ባዶ ምዕራፍ ይፈጠራል
ምስሎች In line with text ናቸውምስሎች ከቦታቸው ይሸሻሉ
ጽሑፍ በText Box ውስጥ የለምበሳጥን ያለ ጽሑፍ ሲቀየር ሊጠፋ ይችላል
ምስሎች JPG ወይም PNG ናቸውሌላ ዓይነት ምስል ላይታይ ይችላል
ምክር፦ከማሳተምዎ በፊት Preview ተጭነው መጽሐፉን ይመልከቱ፤ ሲስተሙ ያገኘው የምዕራፍ ቁጥር ከመጽሐፍዎ ጋር እኩል መሆኑን ያረጋግጡ።

13. ዲጂታል ምርት መጫን#

ዲጂታል ምርት ገዢው እንደከፈለ የሚያወርደው ፋይል ወይም የሚያገኘው አገናኝ ነው፦ የPDF መጻሕፍት፣ አብነቶች፣ የጥናት ጥቅሎች፣ የዲዛይን ሥራዎች። አንድ ጊዜ ያዘጋጁታል፤ ደጋግመው ይሸጡታል። በStudio ውስጥ Digital products ይክፈቱ፤ New digital product ይጫኑ። ቅጹ አምስት እርምጃዎች አሉት።

እርምጃ 1 · Basics

Digital product Basics፦ ርዕስ፣ አጭር መግለጫ፣ ምድቦችና ቋንቋ(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
ርዕስ፣ አጭር መግለጫ፣ ምድብና ቋንቋ
  • 1Title፦ የምርቱ ስም
  • 2Short tagline (optional)፦ አጭር መግለጫ
  • 3Category፦ ተስማሚው ምድብ (ከታች)
  • 4Language፦ የምርቱ ቋንቋ
ምድብምን ይይዛል
PDF booksየሚወርዱ የPDF መጻሕፍት፣ መመሪያዎችና የሥራ ደብተሮች
Business templatesየንግድ ዕቅዶች፣ ኢንቮይሶች፣ ዋጋ መጠየቂያዎች፣ ደረሰኞች፣ የሰው ኃይል ቅጾች
Excel & Sheets toolsየወጪ መከታተያ፣ የዕቃ መዝገብ፣ የትርፍና የደመወዝ ማስያ
Exam preparationየልምምድ ጥያቄዎች፣ የክለሳ ማስታወሻዎች፣ የሙከራ ፈተናዎች
CV & career kitsየሲቪና የማመልከቻ ደብዳቤ አብነቶች፣ የቃለ መጠይቅ ጥያቄዎች
Social media design packsየCanva ፖስቶች፣ ስቶሪዎች፣ ሜኑዎች፣ የበዓል ማስታወቂያዎች
Language learningየአማርኛ እና እንግሊዝኛ ቃላት፣ የውይይት መመሪያዎች
Ethiopian art & printablesየግድግዳ ሥዕሎች፣ የጥሪ ካርዶች፣ የቀን መቁጠሪያዎች
Other digitalሌላ ማንኛውም ዲጂታል ምርት

እርምጃ 2 · Cover & previews

ሽፋንና የናሙና ምስሎች መጫኛ(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
ሽፋንና ናሙናዎች
  • 1Upload cover፦ በሱቁ የሚታይ ሽፋን
  • 2Add preview፦ ገዢዎች ከመክፈላቸው በፊት የሚያዩት ናሙና (እስከ 8 ምስል)

እርምጃ 3 · What buyers get

ፋይሎች፣ Add a link እና ነጻ ናሙና መጫኛ(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
ፋይሎች፣ አገናኞችና ነጻ ናሙና
  • 1Files (ግዴታ)፦ እስከ 20 ፋይል፣ እያንዳንዱ እስከ 500 MB፦ PDF, Excel, Word, PowerPoint, CSV, EPUB, JPG, PNG, WebP, GIF, TIFF, ZIP
  • 2Add a link፦ የCanva፣ Google Sheets / Docs ወይም Drive አገናኝ፤ ገዢው የሚያየው ከከፈለ በኋላ ብቻ ነው
  • 3Free sample (optional)፦ ማንም ከመግዛቱ በፊት የሚያወርደው ጥቂት ገጽ ወይም አንድ አብነት
ጥንቃቄ፦የአገናኙን ማጋራት anyone with the link ያድርጉት (በCanva፦ Share → Template link)፤ አለበለዚያ ገዢው መክፈት አይችልም። የባለቤትነት መብቱ የእርስዎ የሆነ ሥራ ብቻ ይጫኑ።

እርምጃ 4 እና 5 · ዋጋና መግለጫ

የብርና የዶላር ዋጋ ሳጥኖች፣ Suggest from ETB፣ መግለጫ፣ Publish እና Save draft(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
ዋጋ፣ መግለጫና ማሳተም
  • 1Price (ብር)፦ የብር ዋጋ (LOCAL · ETB)
  • 2Was (ብር)፦ የቀድሞ ዋጋ
  • 3Price ($)፦ የዶላር ዋጋ (INTERNATIONAL · USD)
  • 4Suggest from ETB፦ ከብር ዋጋዎ የዶላር ዋጋ ይጠቁማል፤ መቀየር ይችላሉ
  • 5Description፦ ምን እንደያዘ፣ ለማን እንደሆነና እንዴት እንደሚጠቀሙበት
  • 6Publish፦ ወዲያውኑ ለሽያጭ ያቀርባል
  • 7Save draft፦ ለጊዜው ያስቀምጣል

የጫኗቸው ምርቶች ከቅጹ ሥር ዋጋ (Price)፣ የተሸጠ ብዛት (Sales) እና ሁኔታ (Status) ጋር ይዘረዘራሉ። ዲጂታል ምርቶች ለግምገማ ሳይጠብቁ ወዲያውኑ ይታተማሉ።

14. አካላዊ ዕቃዎች፣ መላኪያና ትዕዛዞች#

አካላዊ ዕቃዎች እርስዎ አሽገው የሚልኳቸው ዕቃዎች ናቸው፦ የታተሙ መጻሕፍት፣ ዘሮች፣ ቅመሞች፣ የእጅ ሥራዎች። በStudio ውስጥ Products ይክፈቱ።

ጥንቃቄ፦በዚህ መመሪያ ቀን የአካላዊ ዕቃዎች ሽያጭ ገና አልተከፈተም፤ በሱቁ ላይ Coming soon ተብለው ይታያሉ፤ ገዢዎች ገና ሊገዟቸው አይችሉም። ዕቃዎችዎን፣ ዋጋዎችንና የመላኪያ ዋጋን አሁኑኑ አዘጋጅተው ማስገባት ይችላሉ፤ ሽያጩ ሲከፈት ይቀርባሉ። ከዚህ በታች ያለው የትዕዛዝ አላላክ መመሪያ ለዚያ ጊዜ ነው።

በመጀመሪያ፦ የመላኪያ ዋጋ (Shipping rates)

Shipping rates፦ Ships from፣ የሀገር ውስጥና የዓለም አቀፍ መላኪያ ዋጋ፣ Save rates እና New product(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
Shipping rates እና Your products
  • 1Ships from፦ ዕቃው የሚላክበት አገር
  • 2Local shipping (ብር / ETB)፦ በChapa ለሚከፍሉ
  • 3International shipping ($ / USD)፦ በካርድ ለሚከፍሉ
  • 4Save rates፦ ያስቀምጣል። ነጻ መላኪያ ለማድረግ 0 ያስገቡ
  • 5New product፦ አዲስ ምርት (ከታች)
ማስታወሻ፦የመላኪያ ዋጋ በአንድ ትዕዛዝ አንድ ጊዜ የሚከፈል ቋሚ ክፍያ ነው። ኮሚሽንና 3% ማስኬጃ በዕቃውም በመላኪያውም ዋጋ ላይ ይታሰባሉ።

አዲስ ምርት (New product)

New product ቅጽ፤ አሥሩ ምልክቶች ተቆጥረው(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
New product ቅጽ
  • 1የመላኪያ ዋጋ ካላስቀመጡ ይህ ማሳሰቢያ ይታያል
  • 2Title፦ የዕቃው ስም
  • 3Category፦ ምድብ (ለምሳሌ Herbs & Spices)
  • 4Stock፦ በእጅዎ ያለው ብዛት
  • 5Arkive kingdom link፦ ለምሳሌ ዘር ከሆነ Plants
  • 6Price ($)፦ የዶላር ዋጋ
  • 7Price (ብር)፦ የብር ዋጋ
  • 8Description፦ ምን እንደሆነና ገዢው ምን እንደሚደርሰው
  • 9Photos፦ እስከ 6 ፎቶ
  • 10Create & submit for review፦ ለግምገማ ማስገባት

አዲስ አካላዊ ዕቃ ከመታየቱ በፊት በአስተዳዳሪ ይገመገማል። ከጸደቀ በኋላ ሁኔታው Live ይሆናል፤ የዋጋና የብዛት ለውጥ ወዲያውኑ ይታያል።

ትዕዛዞችን መላክ (Orders)#

Studio Orders ገጽ፦ To ship ርዕስና ባዶ ዝርዝር(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
Studio · Orders
  • 1To ship፦ የተከፈሉና እርስዎን የሚጠብቁ ትዕዛዞች
  • 2ምንም የሚጠብቅ ከሌለ ይህ መልእክት ይታያል
  1. ሽያጩ ሲከፈት የተከፈለበት ትዕዛዝ በTo ship ይታያል፤ የገዢው የመላኪያ አድራሻ እዚያው ይገኛል።
  2. ዕቃውን አሽገው ይላኩ።
  3. Carrier (optional) ላይ የላኪውን ድርጅት (ለምሳሌ EMS፣ DHL፣ Ethiopost)፣ Tracking number (optional) ላይ የመከታተያ ቁጥሩን ያስገቡ።
  4. Mark shipped ይጫኑ፤ ገዢው ኢሜይል ይደርሰዋል፤ ትዕዛዙም ወደ Shipped ዝርዝር ይዛወራል።

15. የደረሱ ድጋፎች (Tips)#

ደጋፊዎች የሰጡዎትን ድጋፍና መልእክቶች በStudio ውስጥ Tips ላይ ያገኛሉ። ከእያንዳንዱ ድጋፍ 80% የእርስዎ ነው፤ ከሌላው ገቢዎ ጋር በገቢ ክፍያ ይላካል።

Studio Tips ገጽ፦ Share my tip link እና መግለጫዎች(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
Studio · Tips
  • 1Share my tip link፦ የድጋፍ አገናኝዎን ማጋራት
  • 280% የእርስዎ መሆኑን የሚያብራራ
  • 3ድጋፍ ሲደርስ እዚህ ይዘረዘራል
ምክር፦1 ድጋፍ ሲደርስዎ Loved፣ 10 ሲደርስዎ Patron Favourite ስኬቶችን ያገኛሉ።

16. ዕቅዶች፣ Spotlight እና ስኬቶች#

ዕቅድዎ ከፍ ሲል አርካይቭ የሚወስደው ኮሚሽን ይቀንሳል። በStudio ውስጥ Plans & growth ይክፈቱ።

Plans and growth አናት፦ የአሁኑ ዕቅድ፣ ኮሚሽንና ደረጃ(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
የአሁኑ ዕቅድዎና ደረጃዎ
  • 1የአሁኑ ዕቅድዎ (እዚህ Free plan)
  • 2Commission on your next sale፦ በሚቀጥለው ሽያጭ የሚታሰበው ኮሚሽን
  • 3ደረጃዎና የልምድ ነጥብዎ (Level እና XP)

ዕቅድ መምረጥ (Choose your plan)

ሦስቱ ዕቅዶች፦ Free፣ Pro 299 ብር፣ Premium 499 ብር እና የመክፈያ ቁልፎች(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
Free፣ Pro እና Premium
  • 1Free፦ የአሁኑ ዕቅድ
  • 2Pro፦ 299 ብር በወር
  • 3Premium፦ 499 ብር በወር
  • 4Go Pro፦ በChapa መክፈል
  • 5Go Premium፦ በChapa መክፈል
FreeProPremium
የዕቅድ ዋጋ (30 ቀን)0 ብር299 ብር499 ብር
ኮሚሽን ከእያንዳንዱ ሽያጭ35%15%10%
ከኮሚሽን በኋላ የሚቀርልዎ65%85%90%
የማረጋገጫ ምልክትየለምሰማያዊወርቃማ
የፕሮፋይልና የሱቅ ገጽታመደበኛሰማያዊ ብርሃንየእሳት አኒሜሽን፣ ወርቃማ ቀለበት፣ «On fire» መለያ
በContributors ገጽ ቅደም ተከተልመደበኛከFree በላይከPro እና Free በላይ
ተጨማሪ የልምድ ነጥብ (XP)የለም+300+1000
ማስታወሻ፦የዕቅዱ ዋጋ በብር በChapa በወር ይከፈላል። በራሱ አይታደስም፤ በፈለጉ ጊዜ ያድሱታል፤ የገዙት ቀናት በዕቅድዎ ላይ ይደመራሉ። ዕቅዱ ሲያልቅ ወደ Free ይመለሳሉ። እያንዳንዱ ሽያጭ በተፈጸመበት ቀን በነበረው መጠን ይታሰባል፤ መደበኛው መጠን በኋላ ከቀነሰ ግን ዝቅተኛው ይቆጠርልዎታል።

Spotlight፦ ጎልቶ መታየት

Spotlight ፕሮፋይልዎን በContributors ገጽ አናት ላይ ያስቀምጠዋል። በየትኛውም ዕቅድ ይሠራል፤ ደግመው ከገዙ ጊዜው ይራዘማል። የሚፈልጉትን ጊዜ መርጠው Spotlight me ይጫኑ።

ሦስቱ የSpotlight አማራጮች፤ እያንዳንዱ Spotlight me ቁልፍ ተቆጥሮ(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
የSpotlight አማራጮች
ቁ.ጊዜዋጋበቀንለምን ይጠቅማል
13 DAYS · LAUNCH BOOST49 ብር16.33 ብርአዲስ ሥራ ሲለቀቅ ወይም ለሳምንቱ መጨረሻ
21 WEEK99 ብር14.14 ብር7 ቀን በአናት
31 MONTH (BEST VALUE መለያ)299 ብር9.97 ብር30 ቀን በአናት፤ በቀን ሲሰላ ርካሹ

ስኬቶችና ደረጃዎች (Achievements)

ከመጻሕፍት፣ ከሽያጭ፣ ከተከታዮች፣ ከድጋፍና ከአንባቢዎች የኮከብ ምዘና የልምድ ነጥብ (XP) ያገኛሉ። ሰባት ደረጃዎች አሉ፦ Seed → Sprout → Sapling → Acacia → Cedar → Baobab → Ark Legend (15,000 XP)። ደረጃዎና ስኬቶችዎ በሱቅዎ የሕዝብ ገጽ ላይ ይታያሉ።

Achievements፦ 0/18 እና አራት ስኬቶች ተከብበው(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
Achievements፦ 18ቱ ስኬቶች
  • 1የተገኙ ስኬቶች ብዛት (0/18)
  • 2First Chapter፦ የመጀመሪያ ርዕስ
  • 3Bestseller፦ 100 ሽያጭ
  • 4Patron Favourite፦ 10 ድጋፍ
  • 5Golden Flame፦ Premium መሆን
ስኬትመስፈርትስኬትመስፈርት
First Chapterየመጀመሪያ ርዕስ ማሳተምRising Seller10 ሽያጭ
Bookshelf5 ርዕስ ማሳተምBestseller100 ሽያጭ
Living Library20 ርዕስ ማሳተምLovedየመጀመሪያ ድጋፍ
First Saleየመጀመሪያ ሽያጭPatron Favourite10 ድጋፍ
First Downloadየመጀመሪያ ዲጂታል ምርት መሸጥGathering10 ተከታዮች
Template Library5 ዲጂታል ምርት ማሳተምCommunity100 ተከታዮች
Makerየመጀመሪያ አካላዊ ዕቃ መዘርዘርFive Starsከ5 ወይም ከዚያ በላይ ገዢዎች በአማካይ 4.5 ኮከብ
First Parcelየመጀመሪያ አካላዊ ዕቃ መሸጥVerifiedPro መሆን
In the SpotlightSpotlight መግዛትGolden FlamePremium መሆን

17. የሱቅ ቅንብሮች፣ የገቢ ክፍያና ግብር#

በStudio ውስጥ Shop settings ሦስት ክፍሎች አሉት፦ የሱቅና የግል መረጃ፣ Payout details እና Tax details። እያንዳንዱ የራሱ የማስቀመጫ ቁልፍ አለው።

Shop settings፦ ፎቶ፣ የሱቅ ስም፣ አድራሻ፣ Tagline እና About(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
Shop settings
  • 1Profile photo፦ ፎቶ መቀየር
  • 2Shop name፦ የሱቅ ስም
  • 3Shop URL፦ የሱቁ አድራሻ
  • 4Tagline፦ አጭር መግለጫ
  • 5About፦ ስለ ሱቁ
Tax details፦ Tax residency፣ TIN፣ የንግድ ፈቃድ ቁጥርና Save tax details(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
Tax details
  • 1Tax residency፦ ባለ 2 ፊደል የአገር ኮድ (ኢትዮጵያ ET)
  • 2TIN፦ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (8 እስከ 15 አኃዝ)
  • 3Business licence no.፦ የንግድ ፈቃድ ቁጥር
  • 4Save tax details

የገቢ ክፍያ መቀበያ (Payout details)#

Payout details፦ የባንክ አገር፣ Zelle ወይም የባንክ ዝውውር፣ ስም፣ ኢሜይልና Save payout details(ምስሉን በሙሉ መጠን ይክፈቱ)
Payout details (እዚህ ከኢትዮጵያ ውጭ፣ Zelle ተመርጧል)
  • 1I bank in Ethiopia፦ CBE ወይም የባንክ ዝውውር
  • 2I bank outside Ethiopia፦ Zelle ወይም ዓለም አቀፍ ዝውውር
  • 3Zelle፦ በZelle ለመቀበል
  • 4Bank transfer፦ በባንክ ዝውውር
  • 5Account holder's full name፦ ልክ በሒሳቡ ላይ እንዳለ
  • 6Zelle email፦ የZelle ኢሜይልዎ
  • 7Save payout details፦ ያስቀምጣል

ግብር (Tax details)#

ጥንቃቄ፦ይህ የሚመለከተው በኢትዮጵያ ነዋሪ ለሆኑ ሻጮች ብቻ ነው። TIN እና የንግድ ፈቃድ ቁጥር ሁለቱም ካሉ ከገቢ ክፍያዎ 3% ይቀነሳል፤ ከሁለቱ አንዱ እንኳ ከጎደለ 30% ይቀነሳል። ተቀናሹ ከ10,000 ብር (አገልግሎት) ወይም ከ20,000 ብር (ዕቃ) በላይ በሆኑ ክፍያዎች ላይ ብቻ ሲሆን ለመንግሥት ይገባል። በዚህ መመሪያ ቀን ተቀናሹ ገና አልተጀመረም።

ዓመታዊ ሽያጭዎ ከ2,000,000 ብር ካለፈ የVAT ምዝገባ ግዴታ ነው። የገቢ ግብርዎ የራስዎ ኃላፊነት ነው፤ ይህ የግብር ምክር አይደለም።

የላቀ መረጃ#

18. የገቢ ስሌትና ትክክለኛውን ዕቅድ መምረጥ#

ገዢው የዝርዝሩን ዋጋ ይከፍላል፤ ኮሚሽኑንና የክፍያ ማስኬጃውን ሻጩ ይሸከማል። ስሌቱ ለዶላርም ለብርም አንድ ነው።

የሚደርስዎ = ዋጋ − (ዋጋ × የዕቅድዎ ኮሚሽን) − (ዋጋ × 3%)

ከአንድ ሽያጭ የሚደርስዎ

ዋጋዕቅድኮሚሽንማስኬጃ 3%የሚደርስዎከዋጋው
$24.00Free 35%$8.40$0.72$14.8862%
$24.00Pro 15%$3.60$0.72$19.6882%
$24.00Premium 10%$2.40$0.72$20.8887%
799 ብርFree 35%279.65 ብር23.97 ብር495.38 ብር62%
799 ብርPro 15%119.85 ብር23.97 ብር655.18 ብር82%
799 ብርPremium 10%79.90 ብር23.97 ብር695.13 ብር87%

ዕቅዱ ራሱን የሚከፍለው መቼ ነው?

ዕቅድ ሲያሳድጉ የሚቆጥቡት የኮሚሽን ልዩነቱን ብቻ ነው። የዕቅዱ ወርሃዊ ዋጋ በዚያ ልዩነት ሲካፈል መነሻውን ያገኛሉ።

ከወደየሚቆጥቡትተጨማሪ የዕቅድ ዋጋራሱን የሚከፍልበት ወርሃዊ ሽያጭ
FreePro20%299 ብር1,495 ብር
FreePremium25%499 ብር1,996 ብር
ProPremium5%200 ብር4,000 ብር
በወር የሚሸጡት (ጠቅላላ)ትርፋማው ዕቅድ
ከ1,495 ብር በታችFree
ከ1,495 እስከ 4,000 ብርPro
ከ4,000 ብር በላይPremium

«ወርሃዊ ሽያጭ» ገዢዎች በ30 ቀን የከፈሉት ጠቅላላ ነው። የዶላር ሽያጭም ቁጠባውን ይጨምራል፤ በዶላርም የሚሸጡ ከሆነ የዶላር ሽያጭዎን በዕለቱ የምንዛሪ ተመን በብር አስልተው ከብር ሽያጭዎ ጋር ይደምሩት። ከድጋፍ (Tips) የሚደርስዎ ግን ሁልጊዜ 80% ነው፤ በዕቅድዎ አይለወጥም።

ራሱን የሚከፍልበት ወርሃዊ ሽያጭ = ተጨማሪ የዕቅድ ዋጋ ÷ የሚቆጥቡት የኮሚሽን ልዩነት

በዶላርም የሚሸጡ ከሆነ ምሳሌ፦ በወር $40 (በካርድ) እና 1,000 ብር (በChapa) የሚሸጡ ከሆነ፣ በዕለቱ ተመን $1 = 150 ብር ቢሆን ጠቅላላው 7,000 ብር ይሆናል (6,000 + 1,000)። ይህ ከ4,000 ብር በላይ ስለሆነ Premium ይመረጣል፦ ከFree ጋር ሲነጻጸር 7,000 × 25% = 1,750 ብር ይቆጥባሉ፤ የዕቅዱ ዋጋ 499 ብር ስለሆነ በወር 1,251 ብር ያተርፋሉ። ተመኑ ምሳሌ ብቻ ነው፤ የዕለቱን ተመን ይጠቀሙ።

ምሳሌ፦ በወር 10 ቅጂ በ799 ብር (ጠቅላላ 7,990 ብር)

ዕቅድከሽያጭ የሚደርስዎየዕቅድ ዋጋየተጣራ ገቢ
Free4,953.80 ብር0 ብር4,953.80 ብር
Pro6,551.80 ብር299 ብር6,252.80 ብር
Premium6,951.30 ብር499 ብር6,452.30 ብር
ምክር፦ሰማያዊ ወይም ወርቃማ የማረጋገጫ ምልክት የገዢዎችን እምነት ስለሚጨምር ከመነሻው በፊትም ማሳደግ ሊጠቅም ይችላል።

19. ችግር ፈቺ#

ችግሩምክንያቱመፍትሔው
ከፍዬ መጽሐፉ በላይብረሪዬ የለምበሌላ ኢሜይል ገብተዋል ወይም ክፍያው ገና እየተረጋገጠ ነውበክፍያው ጊዜ ባስገቡት ኢሜይል ይግቡ፤ ጥቂት ደቂቃ ቆይተው ገጹን ያድሱ፤ በMy orders ትዕዛዙን ይመልከቱ።
Buy now የለም፤ Coming soon ይላልፋይል ገና አልተጫነምሻጩ ፋይሉን እስኪጭን ይጠብቁ።
የክፍያ ቁልፉ አይሠራምኢሜይል አልገባም ወይም ምርቱ በዚያ ገንዘብ ዋጋ የለውምኢሜይል ያስገቡ፤ ከቁልፉ ሥር ያለውን ምክንያት ያንብቡ።
ገንዘብ ተቀንሶብኛል ግን ትዕዛዝ አልታየምክፍያው ገና እየተረጋገጠ ነው ወይም በሌላ ኢሜይል ተከፍሏልጥቂት ደቂቃ ቆይተው የMy orders ገጹን ያድሱ፤ ከቀጠለ የChapa ደረሰኝዎን ይዘው thedove@thearkiveofnoah.com ያሳውቁ። እንደገና አይክፈሉ።
ክፍያው አልተሳካምየካርድ ወይም የChapa ሒሳብ ችግርጋሪዎ አልጠፋም፤ ሌላ የክፍያ መንገድ ይሞክሩ። ገንዘብ ካልተቀነሰ ምንም አልተከፈለም።
ገንዘቤ ይመለስልኝዲጂታል ግዢ በመርህ የመጨረሻ ነውፋይሉ የተበላሸ፣ ከመግለጫው የተለየ ወይም ያልደረሰ ከሆነ thedove@thearkiveofnoah.com ይጻፉ፤ ይስተካከላል ወይም ገንዘቡ ይመለሳል።
የይለፍ ቃሌን ረሳሁየይለፍ ቃሉ አይታወስምበመግቢያ ገጹ Forgot? ይጫኑ፤ ከገቡ ደግሞ Password & security።
መጽሐፉ ገጽ በገጽ ሳይሆን ወደ ታች ይወርዳልነባሪው ሁነታ Scroll ነውየሁለት ዓምድ ምልክቱን ተጭነው Page ይምረጡ።
የማውረጃ አገናኙ አይሠራምአገናኙ ከ10 ደቂቃ በኋላ ያልፋልፋይሉን እንደገና ይጫኑ፤ አዲስ አገናኝ ይፈጠራል።
ከ100 ዝርያ በላይ ማየት አልቻልኩምየነጻ ገደብArkive Pass ይግዙ።
የWord መጽሐፌ ማውጫ ባዶ ነውየHeading ስታይሎች አልተጠቀሙምየማረጋገጫ ዝርዝሩን ይከተሉ፤ እንደገና ይጫኑ።
PDF መጽሐፍ ለንባብ አይቀበልምPDF ለአንባቢው አይፈቀድምወደ EPUB ይቀይሩ፤ ወይም በPDF books ምድብ እንደ ዲጂታል ምርት ይሽጡ።
ገዢ የCanva/Google አገናኙን መክፈት አልቻለምማጋራቱ የተገደበ ነውማጋራቱን anyone with the link ያድርጉት።
አካላዊ ዕቃዬ «Coming soon» ይላልየአካላዊ ዕቃዎች ሽያጭ ገና አልተከፈተምምርቱን አዘጋጅተው ይጠብቁ፤ Shipping rates ማስቀመጥዎን አይርሱ።
የመጀመሪያ የገቢ ክፍያዬ ዘገየየባንክ መረጃ አልተሞላምPayout details ይሙሉ።

20. ደኅንነትና ግላዊነት#

  • የይለፍ ቃልዎን ለማንም አይስጡ። የአርካይቭ ሠራተኞች የይለፍ ቃልዎን ወይም የክፍያ ኮድዎን አይጠይቁም።
  • የማጭበርበሪያ መልእክቶችን ይጠንቀቁ፦ «አካውንትዎ ታግዷል»፣ «ክፍያ ያረጋግጡ» ወይም «አስተዳዳሪ ነኝ» የሚሉ መልእክቶች ከደረሱ አገናኙን አይጫኑ፤ ድረ-ገጹን ራስዎ ከፍተው ይግቡ።
  • ገንዘብ የሚከፍሉት በChapa ወይም በStripe ገጽ ላይ ብቻ ነው፤ የካርድ ቁጥርዎን በኢሜይል ወይም በመልእክት አይላኩ።
  • ከመክፈልዎ በፊት የአድራሻ መስመሩ thearkiveofnoah.com፣ checkout.chapa.co ወይም checkout.stripe.com መሆኑን ያረጋግጡ።
  • ከከፈሉ በኋላ የChapa ደረሰኝዎን (View Chapa receipt) ይመልከቱ፤ መጠኑና የትዕዛዝ ቁጥሩ በMy orders ካለው ጋር መመሳሰሉን ያረጋግጡ።
  • በድጋፍ መልእክት ላይ የሚጽፉት ለሁሉም ይታያል፤ ስልክ ወይም አድራሻ አይጻፉ።
  • የባንክና የግብር መረጃዎ በግል ይቀመጣል፤ በሕዝብ ገጽ ላይ አይታይም።

አካውንቴ የተሰረቀ ይመስለኛል

  1. ወዲያውኑ በPassword & security የይለፍ ቃልዎን ይቀይሩ (ካልገቡ በForgot?)።
  2. በMy orders እና በStudio ያልታወቁ ለውጦች ካሉ ይመልከቱ። ሻጭ ከሆኑ በተለይ Payout details (የባንክ ሒሳብ ቁጥር) እንዳልተቀየረ ያረጋግጡ፤ ከተቀየረ ወዲያውኑ ያስተካክሉና ያሳውቁ።
  3. በምናሌው Contact አርካይቭን ያሳውቁ።

ሙሉ ደንቦቹን በገጹ ግርጌ Terms እና Privacy ላይ ያገኛሉ።

21. የቃላት መፍቻና እርዳታ#

በስክሪኑ ላይትርጉሙ
Sign in / Sign up / Sign outመግባት / መመዝገብ / መውጣት
Shop / The Exchangeሱቅ / የሁሉም ሱቆች ገበያ
Search / Filters / Sort byመፈለግ / ማጣሪያ / መደርደር
Add to cart / Buy nowወደ ጋሪ መጨመር / አሁን መግዛት
Coming soonበቅርቡ ይቀርባል
Read onlineበመስመር ላይ ማንበብ
Price / Wasዋጋ / የቀድሞ ዋጋ
optional / Requiredግዴታ ያልሆነ / ግዴታ
Upload / Downloadመጫን / ማውረድ
Draft / Publishedረቂቅ (የማይታይ) / የታተመ (የሚታይ)
Publish / Previewማሳተም (ለሽያጭ ማቅረብ) / ቅድመ ዕይታ
Scroll / Pageሳይቋረጥ ወደ ታች / ገጽ በገጽ
Bookmark / Highlightዕልባት / ማድመቅ
Stock / Shippingበእጅ ያለ ብዛት / መላኪያ
Commissionኮሚሽን፤ አርካይቭ ከሽያጭ የሚወስደው ድርሻ
Processingየክፍያ ማስኬጃ (3%)
Payment / Payoutገዢ የሚከፍለው ክፍያ / ለሻጭ የሚላክ የገቢ ክፍያ
Balanceቀሪ ሒሳብ
Tip / Supporterድጋፍ / ደጋፊ
Followers / Verifiedተከታዮች / የተረጋገጠ
Level / XPደረጃ / የልምድ ነጥብ
Ratingየኮከብ ምዘና
Spotlightበአናት ጎልቶ መታየት
TINየግብር ከፋይ መለያ ቁጥር

እርዳታ ማግኘት

ያልተመለሰ ጥያቄ ካለዎት ከገጹ በላይ Contact ተጭነው አርካይቭን ያግኙ። ይህ መመሪያ ሁልጊዜ ከገጹ ግርጌ ባለው User guide አገናኝ ይገኛል።